Items related to ግዕዝ ከ ሀ እስ&...

ግዕዝ ከ ሀ እስከ ፐ ለጀማሪዎች - All-in-One: ቁጥር ከ ፩ እስከ ፻፼: 1 - Softcover

Berhanu, Nigussie

 
9798242590755: ግዕዝ ከ ሀ እስከ ፐ ለጀማሪዎች - All-in-One: ቁጥር ከ ፩ እስከ ፻፼: 1

Synopsis

ከ ሀ እስከ ፐ እና ከ፩ እስከ ፻፼፡ የግዕዝ ፊደሎች እና ቁጥሮች ለጀማሪዎች!

በኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ልዩ በሆነው የግዕዝ ፊደላት እና የቁጥር ሥርዓት - ከ ሀ እስከ ፐ እና ከ፩ (አንድ) እስከ ፻፼ (አንድ ሚሊዮን) ድረስ የኢትዮጵያ የጥበብ መጀመሪያ ጉዞዎን ከኛ ጋር ይጀምሩ!

ይህ ባለ ሙሉ ቀለም የመማሪያ መጽሐፍ ከ፪ እስከ ፬ (2-4) ዓመት ለሆኑ፣ በተለየ ሁኔታ የተዘጋጀ ቢሆንም ለታዳጊ ሕፃናት፣ ትናንሽ ልጆች፣ አዋቂዎች፣ ከአገር ውጪ ለሚኖሩ የሐበሻ ዲያስፖራ ቤተሰቦች እና ለአማርኛ፣ ግዕዝ እና ኢትዮጵያዊ ለሆነ አጠቃላይ ዕውቀት ፍላጎት ላላቸው በማንኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የተዘጋጀ ድንቅ መማሪያ ነው።

በቀን መቁጠሪያዎች፣ በሃይማኖታዊ የእጅ ጽሑፎች እና በባሕላዊ ወጎች ውስጥ ለዘመናት ጥቅም ላይ የዋለውን የተሟላውን የኢትዮጵያ የግዕዝ ፊደላት እና የቁጥር ሥርዓት በጥንቃቄ ያስተምራል። እያንዳንዱ ገጽ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ነፍስ ያላቸው እስኪመስል ድረስ አጉልቶ እና አሳምሮ ለዕይታ ያቀርባቸዋል፡፡

  • ለተግባራዊ ልምምድ የሚሆኑ ሰንጠረዦች
  • በቀላሉ ለመረዳት ያመች ዘንድ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ መግለጫዎች እና መመሪያዎች
  • አዋቂዎች ልጆቻቸውን ወይም ታናናሾቻቸውን እያስጠኑ ለራሳቸውም የሚሆኑ ዕውቀት የሚገበዩባቸው አጠቃላይ ዕውቀቶች
ይህ መጽሃፍ ለመማሪያነት ብቻ ሳይሆን ለመዝናኛነትም እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ በስጦታም መልክ ለሌሎች ቢያበረክቱት የማያውቁትን ከማሳወቅ ባሻገር ግዕዝን እና ኢትዮጵያን ሌሎችን ከማስተዋወቅ አንጻር ለሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ይኮሩበታል፡፡

ታዳጊዎች የቅድመ ቁጥር ክህሎቶችን እያዳበሩ ባህላዊ ኩራትን ይገነባሉ፤ ትልልቅ ልጆች እና አዋቂ ጀማሪዎች ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ አጠቃላይ እና አስደናቂ ግንዛቤዎችን ጨምሮ ስለግዕዝ ሆሄያት (ፊደላት) እና ቁጥሮች ጠንካራ መሠረት እንዲያገኙ ለሚከተሉት ሁሉ እንዲስማማ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡
  • ከቅይጥ ዘር የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን (ሃበሾች) እና ተጨማሪ ቋንቋ ተናጋሪ ልጆችን የሚያሳድጉ የሃበሻ ቤተሰቦች፤
  • ከ ከ፪ እስከ ፬ (2 – 4) ዓመት ዕድሜ የሚገኙ እና በዓዋቂዎች ክትትል ሥር የሚገኙ፣ ትምሕርት ያልጀመሩ ሕፃናት፤
  • በማንኛውም ዕድሜ ላይ የሚገኙ የአማርኛ እና የግዕዝ ቋንቋ ወይም ኢትዮጲያዊ ትውፊት አፍቃሪዎች
  • “ጥንታዊት የሰው ዘር መገኛ” በመባል የምትታወቀውን ኢትዮጵያ በስነ-ጽሁፋዊ ዓለም የበለጠ ለመረዳት እና ለመቃኘት የሚጓጓ ማንኛውም ሰው
ይህ የመጀመሪያ ደረጃ የመማሪያ መጽሃፍ ነው፡፡ ከፍ ባሉ ደረጃዎች እስከምንገናኝ ድረስ የኢትዮጵያዊያንን ስነ-ጽሁፍ እና ስነ-ስሌት መሠረታዊ ባሕሪይ ለመረዳት ወደ ትክክለኛው መንገድ መጥተዋልና እንኳን ደስ አለዎት! በትክክለኛው መንገድ ኢትዮጵያን ለመረዳት ከዚህ ይጀምሩ - በኢትዮጵያዊያን ቁጥሮች መቁጠር በኢትዮጲያዊያን ሆሄያት (ፊደላት) የተጻፉ ኢትዮጲያዊ ስነ-ጽሁፎች ማጣጣም ይጀምሩ!

እየተዝናኑ የሚማሩበት እና የሚያስተምሩበት ማዕድ እንዲሆንልዎ ልባዊ ምኞታችን ነው፡፡

ከ ሀ እስከ ፐ እና ከ፩ እስከ ፻፼፡ የግዕዝ ፊደሎች እና ቁጥሮች ለጀማሪዎች!

Embark on a captivating journey through Ethiopia’s ancient and unique Ge'ez numeral system – from ሀ እስከ ፐ and ፩ (one) all the way to ፻፼ (one million)! This vibrant, full-color workbook is the perfect introduction for toddlers, young children, Habesha diaspora families, and learners of all ages interested in Amharic, Ge'ez script, and Ethiopian culture. Designed with little hands and curious minds in mind (ideal for ages 2–4 yet accessible to beginners of any age), this book gently teaches the complete traditional Ethiopian numbering system used for centuries in calendars, religious manuscripts, and cultural traditions. Each page brings the alphabets and numerals to life with: Large, bold Ge'ez numerals from ሀ እስከ ፐ and ፩ to ፻፼, including units, tens, hundreds, ten-thousands, and higher combinations up to one million
  • Ample space for hands-on practice
  • Bilingual labels in Amharic and English with simple phonetic guides
  • Delightful, culturally rich illustrations featuring Ethiopia’s iconic and endemic natures.
More than a simple counting book, this is a joyful celebration of Ethiopian heritage and knowledge. Toddlers build early number skills and cultural pride, while older children and adult beginners gain a solid foundation in Ge'ez numerals alongside fascinating insights into Ethiopia’s wildlife, geography, natural phenomena, and ambitious modern achievements. Perfect for:
  • Habesha families raising bilingual and culturally connected children
  • Preschool and early learning environments
  • Amharic and Ge'ez language enthusiasts of any age
  • Anyone eager to explore the Land of Origins through its ancient numbering tradition
Start pronouncing alphabets and counting the Ethiopian way today – from ሀ to ፐ and ፩ to ፻፼ – and fall in love with Ethiopia’s rich past and promising future! Series Note: First book in the Habesha Little Learners Collection – collect the series to master fidel (alphabet), family terms, calendar, holidays, and everyday Ethiopian life.

"synopsis" may belong to another edition of this title.